
በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከሚኒሶታና ሎስ አንጀለስ የቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች ጋር በመሆን በአሜሪካ በሁሉም ግዛቶች ከሚገኙ ከ500 ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ማህበራት ተወካዮች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡
ባሕር ዳር፡ ኅዳር 14/2013 ዓ.ም (አብመድ) ውይይቱ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ በበይነ መረብ በመታገዝ ነው የተካሄደው፡፡
በውይይቱም ባሰፈሩት የአቋም መግለጫ ጽንፈኛው የህወኃት ቡድን ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽት ላይ ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካ የሰላም ደጀን በሆነው በሰሜን እዝ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመውን ጫፍ የረገጠ የሀገር ክህደት ጥቃት እንዲሁም ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም በማይካድራ እና በሌሎች አካባቢዎች በግፍ የተፈጸሙ ጥቃቶችን አጥብቀን እናወግዛለን ብለዋል።
መንግስት ተገዶ የገባበትን የህግ ማስከበር ዘመቻ በአሸናፊነት ለመወጣት የሚያደርግዉን ጥረት እንደግፋለንም ነው ያሉት።
የመከላከያ ሰራዊት የጀግንነት ቆራጥ ተጋድሎ አድንቀዋል፤ የህወሃት ፀረ ህዝብ እና ፀረ-ሰላም ቡድን አከራካሪው ተመቶ እስኪሸነፍ ድረስ የሞራል እና የቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊት አጋርነታችንን እንገልጻለን ብለዋል።
የዘረኛና ፋሽስት የህወሃት ቡድኑን የፕሮፓጋንዳ እና የተላላኪዎቹን የሀሰት ወሬ ዘመቻ ለማጋለጥ እና ትክክለኛውን የቡድኑን ማንነት ለዓለም ሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች፣ ለዓለም ዓቀፉ ማኅበረሰብ፣ ለወዳጅ ሀገሮች መንግስታት እና ለውሳኔ ሰጪ አካላት ለማሳወቅ በተደራጀ መንገድ ለመስራት መወሰናቸውንም ተናግረዋል፡፡
አሸባሪው ሕወኃት በሀገር ወዳዱ የትግራይ ህዝብ ስም የሚያካሂደውን የፖለቲካ ንግድ እንደሚያወግዙ ገልፀው የትግራይ ህዝብ ከመላው ኢትዮጵያውያን ወንድም እና እህት ጋር ሆኖ ይህን ቡድን እንዲታገል ጥሪ እንደሚያቀርቡም ገልጸዋል፡፡
የአሜሪካ የህግ መወሰኛ እና የህግ አስፈፃሚ አካላት፣ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት እና ሌሎች መንግስታት ሁኔታውን በሚገባ አውቀው አሸባሪውን ትህነግ ወደ ህግ በማቅረብ ረገድ ሚናቸውን እንዲወጡ እንደዜጋ የተቀናጀ እና የተናበበ ሰራ ተግተው እንደሚሰሩም መልዕክታቸውን ማስተላለፋቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በይፋዊ ገጹ አስታውቋል።
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ