በፅንፈኛው የትህነግ ጁንታ ላይ እየተወሰደ ያለውን የህግ ማስከበር እንቅስቃሴ እንደሚደግፉ በጅቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ገለጹ።

281
በፅንፈኛው የትህነግ ጁንታ ላይ እየተወሰደ ያለውን የህግ ማስከበር እንቅስቃሴ እንደሚደግፉ በጅቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ገለጹ።
ባሕር ዳር፡ ኅዳር 10/2013 ዓ.ም (አብመድ)
በጅቡቲ የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ በጅቡቲ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋር የልማት ማኅበራት፣ የመረዳጃ ማኅበሮች፣ የእምነት ተቋማትና የነዋሪዎች ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል፡፡
መንግስት በፅንፈኛውና ህገወጡ የህወሓት ጁንታ ላይ እየወሰደው ስለሚገኘው የህግ ማስከበር እንቅስቃሴ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡
አምባሳደር ብርሃኑ የለውጥ ነፋስ በገሪቱ ከነፈሰበት መጋቢት 2010 ዓ.ም ጀምሮ የህወሓት ጁንታ የለውጡን ሂደት ለማደናቀፍ በማለም በትግራይ ክልል የታጠቀ ህገወጥ ኃይል ማደራጀቱን ገልጸዋል።
እንዲሁም በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ፅንፈኛ ቡድኖችን አሰልጥኖ በማሰማራትና ድጋፍ በማድረግ በርካታ ዜጎች እንዲፈናቀሉ፣ ህይወታቸው እንዲያልፍና ንብረት እንዲወድም ያደረገ እኩይ ድርጅት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የማፍያ ባህሪ የተላበሰው ጁንታው ቡድን፣ የፌዴራል መንግስትን የይቅርታ መርህንና የሰላም ጥረቶችን እንደ ድክመት በመቁጠር በቆየው የማፊያና የስግብግብነት ባህሪው ጥግ መያዙንም ተናግረዋል፡፡
ይባስ ብሎም ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ምሽት ለሁለት አስርት ዓመታት በትግራይ ክልል የሀገሩንና የህዝቡን ሰላም ሲጠብቅ በኖረው የሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊታችን ላይ አረመኔያዊ ጥቃት ሰንዝሯል፤ የሀገር ሉዓላዊነትና የሀገር ክብር ላይ የተቃጣ የሀገር ክህደት ወንጀል መፈፀሙን አምባሳደሩ አስረድተዋል፡፡
ይህንን ተከትሎም መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስከበር እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ ገልጸዋል አምባሳደሩ፤ እርምጃውም ወንጀለኞችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለፍርድ የማቅረብ፣ የሀገር ህልውናን የማረጋገጥና የትግራይን ህዝብ ከስግብግቡ ማፊያ ነጻ የማውጣት ግብ ያነገበ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በመድረኩ የተገኙት ተወካዮች በበኩላቸው ጽንፈኛው የሕወሓት ቡድን በመከላከያ ሠራዊት ላይ ያደረሰው አረመኔያዊ ጥቃት የሀገር ክህደት ወንጀል መሆኑን ተናረዋል፤ በጅቡቲ የሚኖረውን ዳያስፖራው ያስቆጣ መሆኑን ገልጸው ድርጊቱን በፅኑ ኮንነዋል፡፡
መንግሥት እየወሰደ ያለውን የህግ ማስከበር እንቅስቃሴ እንደሚደግፉ ተናግረዋል፤ ለመከላከያ ሰራዊቱ የሞራልና ሁሉንተናዊ ድጋፍ በማድረግ ከጎኑ እንደሚቆሙ መናገራቸውን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያሳያል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየአዳማ ከተማና የአዲስ አበባ ዙሪያ ነዋሪዎች በራያ ግንባር ለተሰለፉት ለሐገር መከላከያ፣ለአማራ ልዩ ኃይልና ለሚሊሻ አባላት ድጋፍ አደረጉ።የአዳማ ከተማና የአዲስ አበባ ዙሪያ ነዋሪዎች በራያ ግንባር ለተሰለፉት ለሐገር መከላከያ፣ለአማራ ልዩ ኃይልና ለሚሊሻ አባላት ድጋፍ አደረጉ።
Next articleበመተከል ዞን የንጹኃን ዜጎችን ሕይወት የሚቀጥፉትን ፀረ ሰላም ኃይሎች እስከ መጨረሻው ለመደምሰስ እየተሰራ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት አስታወቀ፡፡