በምዕራብ ወለጋ ዞን በ142 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ፡፡

322
በምዕራብ ወለጋ ዞን በ142 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ፡፡
ባሕር ዳር፡ ኅዳር 09/2013 ዓ.ም (አብመድ) በምዕራብ ወለጋ ዞን በቅርቡ በተደረገው ኦፕሬሽን በ142 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ እንደተወሰዳባቸው፣48 ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉና፣ 64 ደግሞ በህብረተሰቡ ውስጥ ከተበታተኑ በኋላ መያዛቸውን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ አስታውቀዋል፡፡
ለኦነግ ሸኔ አባላት የሎጂስቲክስና ስልጠና ሲሰጡ የነበሩ 1 ሽህ 341 ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ውለዋል ተብሏል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 104 የጽንፈኛው የህወሃት ቡድን አባላት መሆናቸው ተገልጿል፡፡
በምዕራብና በደቡብ ኦሮሚያ አካባቢዎች አንፃራዊ ሰላም እንደሰፈነ ኮሚሽነሩ መግለፃቸውን ኢብኮ ዘግቧል፡፡
Previous articleማህበረሰቡ የአካባቢውን ሰላም ነቅቶ እንዲጠብቅ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አሳሰበ፡፡
Next articleባለፉት 15 ቀናት የሀገርን ሰላም ለማደፍረስ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 287 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፌዴራል ፖሊስ ገለጸ።