መንግስት ህግ ለማስከበር በሚያደርገው ጥረት ሴቶች የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ፡፡

650

ባሕር ዳር፡ ኅዳር 05/2013 ዓ.ም (አብመድ) መንግስት እየወሰደ ባለው ህግ የማስከበር ስራ ሴቶች የቀደምት እናቶችን ተጋድሎ በማስቀጠል የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ የአማራ ሴቶች ማህበር ሊቀመንበር ወይዘሮ ትብለጥ መንገሻ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ከአብመድ ጋር ቆይታ ያደረጉት የአማራ ሴቶች ማሕበር ሊቀመንበር ወይዘሮ ትብለጥ መንገሻ ዘራፊውና ከሃዲው የህወሓት ቡድን ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ላይ ክህደት ከመፈጸሙ በፊትም በሃገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በንጹኅን ዜጎች ላይ ጥቃት ሲፈፅም መቆቱን አስታውሰዋል፡፡

የህወሃት ቡድን በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በመተከል ዞን ፣በኦሮሚያ ክልል ወለጋ፣ በጉራፈርዳ እና በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች በነበረው ጥቃት የችግሩገፈት ቀማሽ ሴቶች፣ ህጻናትና አካል ጉዳተኞች መሆናቸውንም ገልፀዋል፡፡

አሁንም ጉዳት እየደረሰባቸውና ለችግር እየተጋለጡ የሚገኙ በተለይ ህጻናት፣ ሴቶች፣ አረጋውያንና አካል ጉዳተኞች በመሆናቸው የትግራይም ሆነ የአማራ ክልል ሴቶች በህብረት ሊሰሩ እንደሚገባ ወይዘሮ ትብለጥ አሳስበዋል፡፡

ከሀዲው የትህነግ ቡድን ሃገር የማፍረስና ህዝቦችን የመነጣጠል ተልዕኮ አንግቦ እየተንቀሳቀሰ ቢሆንም ይህ ህልሙ እንዳይሳካ ለማድረግ ሴቶች የቀደምት እናቶችን ተጋድሎ በማስቀጠል የህወሃትን ቡድን ለመንግስት አጋልጦ በመስጠት፣ ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ደም በመለገስ፣ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ አጋርነታቸውን ሊያረጋግጡ ይገባል ብለዋል ሊቀመንበሯ፡፡

ዘጋቢ፡- ትርንጎ ይፍሩ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article‹‹ታሪክ ለመጨመር ታሪክን መጠበቅ ››
Next articleበኩር ጋዜጣ ኅዳር 07/2013 ዓ.ም ዕትም