የትግራይ ህዝብ ዘራፊውን ቡድን አሳልፎ በመስጠት ከኢትዮጲያዊያን ጎን እንዲቆም በግንባር ህግን በማስከበር ላይ ያሉ የሚሊሻ አባላት ጥሪ አቀረቡ።

228

ባሕር ዳር፡ ኅዳር 04/2013 ዓ.ም (አብመድ) በሁመራ ግንባር ከሃገር መከላከያና ከአማራ ክልል ልዩ ሃይል ጋር በጥምረት ህግ የማስከበሩን ስራ በጀግንነት እየተወጡ የሚገኙት ሚሊሻዎች የዘራፊው ቡድን በህግ እስኪቀርብ ትግላቸውን እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል::

ዘራፊው የህወሃት ትህነግ ቡድን ወደ ስልጣን ከመጣ ጀምሮ በተለይም በወልቃይት አማራ ተወላጆች ላይ ኢሰብአዊ ድርጊቶችን ሲፈፅም ቆይቷል ብለዋል:: በመከላከያ ሰራዊት እንዲሁም በቅርቡ በማይካድራ ንፁሃን የአማራ ተወላጆች ላይ የፈፀመው ነውረኛ ድርጊትም የክፋቱንና የጭካኔውን ጥግ ያሳየበት ነው ብለዋል።

የሚሊሻ አባላቱ መንግስት ባቀረበው ጥሪ መሰረት ዘራፊውን ቡድን ለህግ ለማቅረብ ወደ ግንባር ዘምተውም በሁመራ ግንባር ድል ማስመዝገባቸውን ተናግረዋል::

የትግራይ ህዝብ ወንድም ህዝብ ነው ዘራፊውን ቡድን አሳልፎ በመስጠት ከኢትዮጲያዊያን ጎን እንዲሰለፍም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል::

ዘጋቢ:-አክሊሉ ምንተስኖት

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleበትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለው ሕግ የማስከበር ሥራ ዒላማ ያደረገው ሕግ የጣሱ ግለሰቦችን ብቻ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ፡፡
Next articleትናንት ምሽት ወደ ባሕርዳር እና ጎንደር ሮኬት ተተኩሷል። በዚህም በአውሮፕላን ማረፊያው አካባቢ መጠነኛ ጉዳት ደርሷል።