ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የትግራይ ህዝብና የፀጥታ አካላት ራሳቸውን ከስግብግቡ የህወሓት ቡድን እንዲያድኑ ጥሪ አቀረቡ፡፡

243

ባሕር ዳር፡ ኅዳር 04/2013 ዓ.ም (አብመድ) ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለትግራይ ህዝብና ለትግራይ የፀጥታ አካላት በትግርኛ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም ቡድኑ በሁሉም አቅጣጫ ተከቦ መውጫ መግቢያ አጥቶ በጣዕረ ሞት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ቡድኑ በየግንባሩ ተገኝቶ አመራር ሊሰጥ በማይችልበት ደረጃ ላይ ይገኛል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የትግራይ ወጣቶችን ያለ ምግብና መጠጥ ለሞትና አካል ጉዳት እየዳረጋቸው እንደሚገኝም አስታውቀዋል፡፡

የትግራይ ህዝብ ልጆቹን እየቀበረ ለሚገኘው ኃይል ሲል መስዋዕትነት ከመክፈል እንዲቆጠብ እና ፈጥኖ እንዲታደጋቸውም ጠይቀዋል፡፡

“የትግራይ ህዝብ የልጆችህ ሞት የእኩዩን ቡድን እድሜ በሰዓታት ወይም በቀናት ከማስረዘም በዘለለ የሚፈይደው የለም” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰው ለአላማ፣ ለሃገርና ለህዝብ እንጂ ለጥፋት ቡድን ብሎ መሞትና አካሉ መጉደል እንደሌለበት አስገንዝበዋል።

“የጁንታውን እድሜ በአጭሩ በመቅጨት ወደ ልማት ሥራዎች እንድንመለስ ተባብረን መስራት ይገባልም” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው፡፡

“የትግራይ ህዝብ የገነባሃትን ሃገር መልሰህ እንድታድናትና ታሪክህን እንድታድስም ሃገርህ ኢትዮጵያ ትጠራሃለች” ሲሉም አሳስበዋል፡፡

በክልሉ የሚገኙ ልዩ ሃይልና የፀጥታ አካላትም ከቀናት ያልበለጠ ዕድሜ ለሌለው ቡድን ሲሉ ህይወታቸውን እንዳያጡም አስገንዝበዋል፡፡

የክልሉ ልዩ ኃይልና የፀጥታ አካላት እጃቸውን ለመከላከያ ሰራዊት በመስጠት በሚቀጥሉት ሁለትና ሶስት ቀናት ራሳቸውን እንዲያድኑ ጥሪ ማቅረባቸውን ፋብኮ ዘግቧል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article“ህፃናትን ወደ ጦርነት መላክ” ሌላው ህገወጡ የትህነግ ቡድን ሊጠየቅበት የሚገባ ወንጀል
Next articleከአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተላለፈ መልዕክት