
ባሕር ዳር፡ ኅዳር 03/2013 (አብመድ) ነዋሪዎቹ በየከተሞቹ አደባባይ በመውጣት ባካሄዱት ሠልፍ መንግስት እየወሰደ ያለውን ህግ የማስከበርና ሀገር የማዳን እርምጃ የህወሃት ጁንታ ሥርዓት እስከሚይዝ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
ስግብግቡ የህወሓት ቡድን በሀገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን እዝ ላይ የፈጸመው ጥቃት የሀገር ክህደት መሆኑን ነዋሪዎቹ ባሰሙት መፈክር ገልጸዋል።
መንግስት የጀመረውን ህግ የማስከበር ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ያስተላለፉት ነዋሪዎቹ በሚችሉት አቅም ሁሉ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን እንደሚደግፉ አስታውቀዋል።
በሌላ በኩል በአፋር ክልል የሠመራ እና ሎግያ ከተማ ነዋሪዎች ለሃገር የመከላከያ ሠራዊት አባላት ያላቸውን አጋርነት ደም በመለገስ አሳይተዋል፡፡
የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የአካባቢው ሀገር ሽማግሌዎች፣ ሃይማኖት አባቶችና ሌሎችም ነዋሪዎች በተሳተፉበት የውይይት መድረክ ላይ በመከላከያ ሠራዊቱ ላይ የተፈጸመውን ጥቃትም አውግዘዋል።
መከላከያ ሠራዊቱ በህወሃት ጁንታ የተጠነሰሰውን ሀገርን የማፍረስ ሴራ በማክሸፍ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና የህግ የበላይነት በማስከበር እያስገኘ ያለውን አኩሪ ገድል ለውይይቱ ተሳታፊዎች ገለጻና ማብራሪያ መሰጠቱን ኢዜአ ዘግቧል፡፡