የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዶ/ር ደብረጸዮን ገብረሚካኤልን ጨምሮ የሌሎችን ግለሰቦች ያለመከሰስ መብት አነሳ፡፡

317

ባሕር ዳር፡ ኅዳር 03/2013 (አብመድ) የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ አቃቤ ህግ በተለያዩ ወንጀሎች የጠረጠራቸውን ግለሰቦች ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምጽ አፀደቀ።

በዚህም መሰረት፦
ዶክተር ደብረጸዮን ገብረሚካኤል
አቶ አስመላሽ ወልደሰንብት
አቶ አባይ ፀሃዬ
ዶክተር አምባሳደር አዲስ ዓለም ቤሌማ
አቶ ጌታቸው ረዳ
አቶ አፅበሃ አረጋዊ
አቶ ገብረ እግዚአብሄር አርአያ እና ሌሎችም ላይ የቀረበው ያለመከሰስ መብት የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምጽ ፀድቋል።

ግለሰቦቹ የተጠረጠሩበት ወንጀሎችም ጦር መሳሪያ ይዞ በማመፅ፣ የሀገር መከላከያን በመውጋት እና በሌሎችም ተያያዥ ወንጀሎች ዋና አድራጊነት ነው መሆኑ ፋብኮ ዘግቧል፡፡

Previous articleወንበዴው እና ስግብግቡ የሕወሓት ቡድን በመከላከያ ሠራዊት ላይ ያደረሰውን ጥቃት የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።
Next article“ህወሐት ሁለት መሳሪያ አላት፤ ክህደት እና ውሸት” አቶ መስፍን ደሳለኝ