
ባሕር ዳር፡ ኅዳር 03/2013 ዓ.ም (አብመድ) የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የስላም ማሰከበር ማሰልጠኛ ተቋም አዛዥ ተወካይ ኮሎኔል ታምራት አንዳርጌ እንደተናገሩት የጉብኝቱ ትኩረት አዲስ የትራንስፖርት እና የጥገና ስራዎችን ለማቋቋም ፣ ማሰልጠኛውን ዘመናዊነቱን ጠብቆ ለማደስ እና አገልግሎት መስጠት የሚችልበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ነው ብለዋል፡፡
የጀርመን ወታደራዊ አታሼ ኮሎኔል ቶማስ ሪበርሊንገ በበኩላቸው ባደረግነው የመስክ ጉብኝት ቀጣይ ላቀድነው እና ለምንሰራቸው ስራዎቻችን ምቹ ሁኔታ ይፈጥርልናል፤የጀርመን እና የኢትዮጵያ ወታደራዊ ትብብርም ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን የሃገር መከላከያ ሚኒስቴር በይፋዊ ገፁ አስነብቧል፡፡