
ባሕር ዳር፡ ኅዳር 03/2013 ዓ.ም (አብመድ) ከሀዲው የህወሃት ቡድን በመከላከያ ሰራዊት ላይ የወሰደውን ጥቃት የሚያወግዝ ሰልፍ በሀዋሳ እየተካሄደ ነው።
በሰላማዊ ሰልፉ ከሲዳማ ክልል ሁሉም ወረዳዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
ሰልፈኞቹ ከሃዲው የህወሃት ጁንታ ቡድን በመከላከያ ሰራዊት ላይ ያደረሰውን ጥቃት የሚቃወሙ መፈክሮችን በመያዝ እያወገዙ ነው።
ከመፈክሮቻቸው መካከልም ‹‹በመከላከያ ሰራዊታችን ላይ ከሃዲው ጁንታ የህወሃት ቡድን የወሰደውን እርምጃ እንቃወማለን፤ከመከላከያ ሰራዊታችን ጎን ሆነን የሚጠበቅብንን ድጋፍ ሁሉ እናደርለን››የሚሉ እና ሌሎች መፈክሮችን አሰምተዋል።
ሰልፈኞቹ ለመከላከያ ሰራዊቱ ያላቸውን አጋርነትም በመግለጽ ላይ መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m