
ባሕር ዳር፡ ህዳር 03/2013 ዓ.ም (አብመድ) ግጭቶችን በማነሳሳት እና በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሽብር ጥቃቶችን በማካሄድ ተልዕኮ በሕወሃት ተላላኪነት የተጠረጠሩ ግለሰቦች በፌደራል እና በአዲስ አበባ ፖሊስ በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ከተለያዩ የኑሮ ዘርፎች የተውጣጡ የተለያዩ ብሔር ተወላጆች ናቸው ፡፡ በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪዎች ጠቅላላ ቁጥር ወደ 150 አካባቢ ነው፡፡ ከነዚህ ተጠርጣሪዎች መካከል ጥቂቶቹ በዋስ ተለቀዋል፡፡
እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ ብዙ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በተሳሳተ መንገድ የእስረኞችን ቁጥር በተመለከተ ሙሉ በሙሉ ያልተረጋገጠ እና የተጋነነ መረጃ እያሰራጩ ይገኛሉ፡፡ የሕግ አስከባሪያችን አሠራር ደንብን የተከተለ እንጂ እንደሚወራው በማንነት ላይ ተመስርቶ ግለሰቦችን የሚያጠቃ አይደለም፡፡
ሁሉም ዓለም አቀፍ አጋሮች እና ተዋንያን በሕወሃት እየተፈፀመ ያለውን የውሸት መረጃ ዘመቻ ልብ እንዲሉ ጥሪ እናቀርባለን ብሏል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m