
ባሕር ዳር፡ ኅዳር 02/2013 ዓ.ም (አብመድ) ለጁንታው እስትንፋስ የነበሩ የነዳጅ ዴፖዎች ፣ የመሳሪያ ማከማቻዎች እና ሌሎች ምርጥ ኢላማዎች የኢትዮጵያ አየር ኃይል ጀቶች ያለምንም ከልካይ እንዳሻቸው እየተመላለሱ አውድመዋቸዋል ብለዋል።
የአየር ኃይል አብራሪዎች የተመረጡ ዒላማዎችን ለመደምሰስ መሣሪያ ጭነው እየሄዱ ሲቪል የሚጎዳ ከመሰላቸው ሳይተኩሱ በመመለስ ነጥሎ የመምታት ስትራቴጂ እየተከተሉ እንደሚገኙም አስገንዝበዋል።
“ጁንታው ጄቶችን እንመታለን የሚለው እድሜውን ሲዋሽ ስለኖረና እየዋሸ ስለሚቀበር ነው፤ በተፈለገ ሰዓት እየተመላለስን ጁንታው ለህግ እስኪሚቀርብ ድረስ ማጥቃታችንን እንቀጥላለን” ማለታቸውን የሃገር መከላከያ ሚኒስቴር በይፋዊ ገፁ አመላክቷል።