ከሀዲው የትህነግ ቡድን ኢትዮጵያን ለማፈራረስ እየሰራ መሆኑን የትግራይ ህዝብ ሊረዳ እንደሚገባ የትግራይ ዴሞክራሲ ፓርቲ አሳሰበ፡፡

387

ባሕር ዳር፡ ህዳር 02/2013 ዓ.ም (አብመድ) የትግራይ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ትዴፓ) የህዝብ ግንኝነት ኃላፊ ሙሉብርሃን ሃይሌ ህገወጡ ትህነግ የትግራይ ህዝብ ያለበትን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መፍታት ባለመቻሉ ወደ ጦርነት ገብቷል ብለዋል፡፡

ዘራፊ ቡድኑ ከህዝብ ጫንቃ የሚወርድበት ጊዜም አሁን በመሆኑ ሁሉን አቀፍ ርብርብ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡ የህገወጡ ትህነግ ቡድን በየቦታው በአደራጃቸው ፀረ-ሰላም ሃይሎች ሀገር በሰላም እንዳትኖር አድርጓል፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔ በመጣስ ህገወጥ ምርጫ አካሂዷል፣በትግራይ ህዝብ ዘንድ ህፃናትን ወደ ጦርነት እየማገደ ነው፤ በመከላከያ ሰራዊት እና በንጹሃን ዜጎች ጥቃት አድርሷል ብለዋል፡፡

ህገወጡ ትህነግ የኢትዮጵያ ህዝቦች ይቅር የማይሉትን አሳፋሪ ድርጊት እንደፈፀመም ተናግረዋል፡፡ የእናት ጡት ነካሹ የትህነግ ቡድን የትግራይን ህዝብ ለእንግልት ዳርጓል የሚሉት የትዴፓ የህዝብ ግንኝነት ኃላፊ በክልሉ በሚያራምደው ፀረ ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች መንቀሳቀስ እንዳልቻሉም አስረድተዋል፡፡

በክልሉ የህገወጡን ቡድን ዓላማ እና አሰራር የማይደግፍ አካል በነፃነት መሰብሰብ፣መናገር እና መደራጀት እንደማይችልም ተናግረዋል፡፡ ዘራፊውና ህገወጡ ትህነግ ባለፉት 27 ዓመታት በዝምድና እና በትውውቅ በአንድ ጀንምበር ሀብት የሚያሸክም ድርጅት መሆኑንም አስርድተዋል፡፡ ይህንን ሴራ ለማጋለጥ የሞከረ አካል ደግሞ ይገደላል፣ይፈናቀላል ነው ያሉት፡፡

የትግራይ ህዝብም ከዘራፊው ቡድን አፈና እና ጭቆና ለመላቀቅ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በመሆን የሚታገልበት ጊዜው አሁን ነው፤የፌዴራል መንግስትም ህግ የማስከበረ ስራውን መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

ትህነግ ለኢትዮጵያ አንድነት ደንታ የሌለው ራስ ወዳድ ቡድን እንደሆነም ገልጸል፡፡ የትግራይ ህዝብም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ተበታትኖ የሚኖረው በኢትዮጵያዊነት በመተማመን ነው የሚሉት ኃላፊው ከዚህ ጦርነት በኃላም ሁሉም የትግራይ ህዝብ ፍትሕ የነገሰባት እና ዋስትና የምትሰጥ ኢትዮጵያን በማሰብ የትህነግ ቡድንን ገርስሶ ለመጣል ሊታገል እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡

ዘጋቢ:- አዳሙ ሽባባው

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleህገ ወጡ የትህነግ መንግሥት እየፈጸመው ያለውን ግፍ ለመላው ዓለም ለማሳወቅ በአማራ ክልል ህዝባዊ የሰላማዊ ሰልፍ በነገው እለት ይካሄዳል፡፡
Next articleመንግስት እየወሰደው ያለውን ህግ የማስከበር እርምጃ ተከትሎ በበይነ መረብ የሚሰራጩ ሐሰተኛ መረጃዎች መበራከታቸውን ቢቢሲ ጠቆመ፡፡