
ባሕር ዳር፡ ህዳር 02/2013 ዓ.ም (አብመድ) የመከላከያ ሚኒስትሩ ቀንአ ያደታ (ዶክተር) በሰጡት መግለጫ በትግራይ ክልል ህግ የማስከበር ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡ ይህ የተደራጀ ጁንታ የሀገር መከላከያን በማጥቃት ሃገርን የማፍረስ እና ሉዓላዊነቷ ላይ አደጋ የጣለ ቡድን መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ነገር ግን የጥፋት ቡድኑ በሀሰተኛ መረጃ ሕዝብን ማደናገር መጀመሩ ተስፋ እየቆረጠ ለመምጣቱ ማሳያ እንደሆነ ነው የመከላከያ ሚኒስቴሩ ያስታወቁት፡፡
ቡድኑ ህግ የማስከበር ስራውን የእርስ በእርስ ጦርነት ለማስመሰል በርካታ የተሳሳቱ መረጃዎችን ይፋ እያደረገ እንደሚገኝም ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።
የትህነግ ቡድን ውሸት ተፈጥሯዊ ስሪቱ መሆኑን ዶክተር ቀንዓ ገልጸዋል። አሁን ላይ በጥፋት ቡድኑ ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉን ጠቅሰዋል።
የትግራይ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ አባላት የዚህ ቡድን ከለላ ከመሆን ይልቅ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት እጃቸውን እንዲሰጡ፣ ካልሆነ ግን መከላከያው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለመደምሰስ እንደሚገደድ የመከላከያ ሚኒስቴሩ አስታውቀዋል።
ዘጋቢ፡ – አንዷለም መናን ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m