
ባሕር ዳር፡ ኅዳር 02/2013 ዓ.ም (አብመድ) የመከላከያ ሚኒስትሩ በሃገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ መግለጫ እየሰጡ ነው።
በመግለጫቸው እንዳመለከቱት የህወሃት የጥፋት ቡድንን ለመደምሰስ የማንንም የውጭ ሃይል ድጋፍ አይፈለግም ብለዋል።
የትግራይ ህዝብ የጥፋት ቡድኑን ሴራ በመገንዘብ ለጉዳት እንዳይዳረግም አሳስበዋል፡፡
ህዝቡ ለሰራዊቱ እያሳየ ያለውን ድጋፍ እንዲያጠናክርም ጥሪ አቅርበዋል።
የመከላከያ ሰራዊት በዘራፊው የህወሃት ቡድን ላይ በርካታ ድል እየተቀዳጀ እንደሚገኝ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡