የትህነግ ሰው በላ ቡድን በማይካድራ በንጹኀን ሰዎች ላይ ጭፍጨፋ ፈጽሟል።

617

ባሕር ዳር፡ ህዳር 02/2013 ዓ.ም (አብመድ) የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ከሃዲው የትህነግ ቡድን ጦርነት ባወጀባቸው አካባቢዎች አቅንቶ ህግ የማስከበሩን እርምጃ ተመልክቷል።

ጦርነቱ ህገመንግስታዊ ስርዓቱን አደጋ ላይ የጣለ እና የሃገር ክህደት በፈፀመው የትህነግ ቡድን ላይ ያነጣጠረ እንደሆነም ከትህነግ ቡድን ነፃ የወጣው ማህበረሰብ አረጋግጧል።

ነገር ግን ማይካድራ በመከላከያ ሰራዊት፣ በአማራ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ በቁጥጥ ስር ከመዋሏ በፊት ጥቅምት 30/2013 ዓ. ም ሌሊት በማይካድራ ህገወጥ ቡድኑ የፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጀል የቡድኑን በአማራ ህዝብ ላይ የለየለትን ጠላትነትና የድርጊቱን አስከፊነት ያሳየ ነበር።

በነበረው የተጠናከረ ጥቃት ሌሎች ይዞታወችን ለቆ ወደ ማይካድራ የገባው የትህነግ ጦር ይደርስበት የነበረውን ከፍተኛ ጥቃት ባለመቋቋሙ መሽጎበት የነበረውን የማይካድራ ይዞታ እንዲለቅም ተገዷል። ማይካድራም ከህገወጥ ቡድኑ ነፃ ሆናለች።

ይሁንና ቡድኑ ከዚህ ቀደም በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች ይፈፅመው የነበረውን የተቀነባበር የሴራ ግጭትና የዜጎች ጭፍጨፋ በማይካደራም ፈፅሞታል። ሰው በላነቱን በአማራ እና በኢትዮጵያዊያን ላይ በተግባር አሳይቷል።

የትህነግ ዘራፊ ቡድን ዓላማ ማስፈጸሚያ የሆኑት ልዩ ሃይል እና ሳምሪ የተባለው ገዳይ ቡድን በማይካድራ ከተማ የሚገኙ ንጹኀን ሰላማዊ ዜጎችን በጂምላ ጨፍጭፏል።

አብመድ በቦታው በመገኘትም በሰው በላው ትህነግ በርካታ ንጹኀን አማራዎች የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸውን አረጋግጧል። በጥቃቱ የሌሎች ብሔር ተወላጆችም ሰለባ እንደሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ዘጋቢ: ወንዳጥር መኮንን

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleህዝቡ በንቃትና በተደራጀ መንገድ አካባቢውን እንዲጠብቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አሳሰቡ፡፡
Next articleየሃገር መከላከያ ሰራዊቱ የማንንም የውጭ ሃይል ድጋፍ ሳይፈልግ የጥፋት ቡድኑን የመደምሰስ ቁመና ላይ መሆኑን የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር ቀንዓ ያደታ ገለጹ።