ህዝቡ በንቃትና በተደራጀ መንገድ አካባቢውን እንዲጠብቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አሳሰቡ፡፡

430

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በይፋዊ ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት “የጁንታው ፀሐይ እየጠለቀች ነው። ይሄንን መርዶ ጁንታው በቁሙ ተረድቶታል። አሁን የሚይዘውን የሚጨብጠውን የሚያጣበት ጊዜ ነው” ብለዋል፡፡

በጣዕር መንፈስ በየቦታውየመጨረሻውን የጥፋት ድግስ ይደግስ ይሆናል። ስለዚህም ሕዝቡ በንቃትና በተደራጀ መንገድ አካባቢውን እንዲጠብቅ አደራ እላለሁ ነው ያሉት።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ወገኖቻችን በየአካባቢያችን
ምንም ዓይነት አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳይደርስባቸው ሁላችንም የወንድሞቻችን ጠባቂ እንሁን ብለዋል።

<< የኢትዮጵያ ጠላት ስግብግቡ ጁንታ ነው። የትግራይ ሕዝብ እንደሌላው ሕዝብ በጁንታው መከራ ያየ ሕዝብ ነው። ጁንታው ለፍርድ እንዲቀርብ የትግራይም ሕዝብ ከመከላከያ ሠራዊት ጋር አብሮ እየተዋጋ ነው።

አካባቢዬን እጠብቃለሁ፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ የመከራ ቀንበር እሰብራለሁ። ጁንታውን ለፍርድ ማቅረብም ቃልኪዳናችን ነው ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Previous article“እየሞትንም ቢሆን እናሸንፋለን!” የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ
Next articleየትህነግ ሰው በላ ቡድን በማይካድራ በንጹኀን ሰዎች ላይ ጭፍጨፋ ፈጽሟል።