“እየሞትንም ቢሆን እናሸንፋለን!” የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ

379

ባሕር ዳር፡ ህዳር 01/2013 ዓ.ም (አብመድ) ዝርዝሩ በፌደራል መንግስት በስፋት እንደሚገለፅ ብንጠብቅም፤ በዛሬዉ እለት ከአረመኔው የትህነግ ቡድን ነፃ በወጣችው በሁመራ አቅራቢያ በምትገኘው ማይካድራ ከተማ ነዋሪ በሆኑ የአማራ ወገኖቻችን ላይ በተሸናፊው የትህነግ ጦር አማካኝነት የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈፅሞባቸዋል።

ቁጥሩ በሂደት ተጣርቶ ይፋ የሚደረግ መሆኑን እያሳወቅን ድርጊቱ በዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) የሚያስጠይቅ ወንጀል መሆኑን እናምናለን ብለዋል የብልጽግና ፓርቲ።

ተሸናፊው ትህነግ በወገኖቻችን ላይ ይሄን አሰቃቂ የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈፀመው በህዝቦች መካከል የእርስ በርስ ጦርነት (Civil War) እንዲቀሰቀስ አስቦ መሆኑን እናውቃለን ነው ያሉት።

ፓርቲው ለአማራ ህዝብ ባስተላለፍት መልዕክት በባህል፣ በሃይማኖት፣ በማህበራዊ ትስስር፣ አልፎም በረዥሙ የአገር ግንባታ ጉዞ ከአማራ ሕዝብ ጋር የጋራ ታሪክ ያለውን የትግራይ ሕዝብ መከታና ጋሻ ሆነህ አስተዋይነትና አብሮነት የምንጊዜም ምርጫህ እንደሆነ ለመላ የኢትዮጵያ ሕዝቦች በተግባር እንድታሳይ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ብለዋል።

የትግራይ ሕዝብ እንደትላንቱ ሁሉ፣ ዛሬም ሆነ ነገ አብሮህ ይኖራል። ዝንታለም ጠላትህ ትህነግና ወገኖችህን የጨረሰው የትህነግ ሰራዊት ነው። ስለዚህ ትህነግ ካጠመደልህ ወጥመድ ሳትገባ፤ የወገኖችህን ደም የምትመልሰው ትህነግንና ገዳይ ሰራዊቱን እስከመጨረሻው በመፋለም መደምሰስ ሲቻል መሆኑን አስገንዝበዋል።

ስለቀጣዩ እርምጃችን ሁኔታወችን እየገመገምን እናሳውቃለን ያሉት ርእሰ መስተዳድሩ ያም ሆነ ይህ ግን ትህነግ ካጠመደው ወጥመድ እንዳትገባለት ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግህን ለአፍታም ቢሆን እንዳትዘነጋ። የወገኖቻችንን ደም የምንመልሰው ትሕነግና ነፍሰ በላ ሰራዊቱን የሚገባቸውን የቅጣት ዋጋ እንዲከፍሉ በማድረግ ነው ነው ብለዋል።

አማራነት የጀግንነት፣ የአብሮነት፣ የአስተውሎት ጥበባዊ ማንነት መገለጫ መሆኑን ዛሬም እንደትላቱ በተግባር እናስመሰክራለን ነው ያሉት።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article‹‹ ራስን በማምለክ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ሲደርስ ከፍተኛ የኃይል መጠን ያለውን ኤሌክትሪክ ያስጨብጣል፤ ህገወጡ ሕወሃት በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ያደረገው ጥቃትም ይህ ነው›› በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የስነ ልቦና መምህር አውግቸው ሽመላሽ
Next articleህዝቡ በንቃትና በተደራጀ መንገድ አካባቢውን እንዲጠብቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አሳሰቡ፡፡