ህገወጡን የህወሃት ቡድንን ለመደምሰስ በግንባር እየታገሉ ለሚገኙ ለመከላከያ ሰራዊት፣ ለአማራ ክልል ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ አባላት የሚውል የደም ልገሳ መርሃ ግብር በወልድያ ከተማ እየተከናወነ ነው፡፡

153

ባሕር ዳር፡ ኅዳር 1/2013 ዓ.ም (አብመድ) የወልድያ ከተማ ነዋሪዎች <<ደማችን ለመከላከያ ሠራዊታችን እና ለአማራ ክልል የፀጥታ አካላት>> በሚል መልዕክት በዛሬው ዕለት ደማቸውን እየለገሱ ነው፡፡

ደም ሲለግሱ ካገኘናቸው ውስጥ ሳንድራ ደምሌ እንዳሉት ደም የለገስኩት ከሰራዊቱ ጋር መሆኔን ለማረጋገጥ ነው፤ ለወደፊትም ደም በሚያስፈልግበት ወቅት ለመለገስ ዝግጁ ነኝ ብለዋል፡፡

የወልድያ ደም ባንክ ኃላፊ ጋሹ ደርበው የወቅቱን ሁኔታ በማገናዘብና የደም እጥረት እንዳይከሰት በዞኑ ሁሉም አካባቢዎች ደም እያሰባሰቡ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የሰሜን ወሎ ዞን ማኅበረሰብ ያለማንም ቀስቃሽነት ደም እየለገሰ መሆኑን ኃላፊው አስረድተዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ባለ አለምዬ – ከወልድያ

Previous articleበትግራይ ክልል እየተከናወነ የሚገኘው ህግን የማስከበር ዘመቻ በታቀደው መንገድ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዐብይ አህመድ አስታወቁ፡፡
Next articleለሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ለአማራ ልዩ ኃይልና ለሚሊሻ አባላት የሚደረገው የደም ልገሳ ቀጥሏል፡፡