
ባህር ዳር፡ ኅዳር 1/2013 ዓ.ም (አብመድ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በትዊተር ገጻቸው እንዳሉት በትግራይ ክልል ህግን የማስከበር ዘመቻው በተቀመጠው እቅድ መሰረት እየተከናወነ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዘመቻው በትህነግ ውስጥ ያለው ጁንታ ትጥቅ ሲፈታና በክልሉ ህጋዊ አስተዳደር ሲመለስ ዘመቻው እንደሚጠናቀቅም አስታውቀዋል፡፡
ህግ የማስከበሩ ርምጃም በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡