
ባሕር ዳር፡ ኅዳር 1/2013 ዓ.ም (አብመድ) የሕብረ-ብሔራዊ አንድነት ችቦውን በመለኮስ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አደን ፋራህ እና የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳደር ሙስጠፌ ሙሐመድ እንዲሁም ሌሎች የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ ባለሥልጣናት ተገኝተዋል።
ዘንድሮ የሚከበረው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችን በዓል ምክንያት በማድረግ ከሚከናወኑ ተግባት መካከል አንዱ ከምሥራቅ ኢትዮጵያ ተነሥቶ በሁሉም ክልል የሚደርስ ሕብረ-ብሔራዊ አንድነት ችቦ ነው።
ችቦው ከሶማሌ ክልል ተነሥቶ በተለያዩ ክልሎች እና ከተማ መስተዳደሮች እንደሚዘዋወር ተገልጿል።
የዘንድሮው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች በዓል “እኩልነት እና ሕብረ-ብሔራዊ አንድነት ለጋራ ብልጽግና” በሚል መሪ መልዕክት ለ15ኛ ጊዜ በፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነት እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስተናጋጅነት በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚከበር ኢብኮ ዘግቧል፡፡