
ባሕር ዳር፡ ኅዳር 1/ 2013 ዓ.ም (አብመድ) በወልቃይት ከተማ ንጉስ እና አካባቢው ለሚገኘው የመከላከያ ሰራዊትና የፀጥታ አካላት ከደምቢያ፣ ላይ አርማጭሆ፣ አይከል ከተማ ጭልጋ ቁጥር አንድ እንዲሁም ከሌሎች በርካታ ወረዳዎች የሰንጋ፣ የበግ እና ፍየል፣ የምግብ እህል ብሎም ዉኃ ድጋፍ ሲደረግ የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት በቦታው ተገኝቶ ተመልክቷል፡፡
ከምዕራብ ደምቢያ ወረዳ አስተዳደር እና ከህዝቡ የተውጣጣ የበግ እና ፍየል እንዲሁም የምግብ እህል ይዘው ያገኘናቸው አስተባባሪ ኮሚቴዎች ዘራፊ ቡድኑን ለመዋጋት መሳሪያ ታጥቆ ግምባር ከመገኘት ባለፈ ይህንን አይነት ድጋፍ አጠናክሮ ማስቀጠል ተገቢ ነው ብለዋል፡፡
መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከሃዲውን እና ዘራፊውን የህወሃት ቡድንን እየተዋጋ ያለውን ሰራዊት በቁሳቁስ እና በሞራል ሊደግፍ እንደሚገባም አስተያየት ሰጭዎቹ ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ፡- አብዮት ከፋለ