
ባሕር ዳር፡ ህዳር 01/2013 ዓ.ም (አብመድ) የውይይቱ ተሳታፊዎች የትህነግ ቡድን በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የፈጸመውን ክህደት አውግዘዋል፤ ቡድኑ ለሰፊው የትግራይ ሕዝብ ጥቅም ሳይሆን ለጥቂት ባለስልጣን ቤተሰቦችና ለራሱ የቆመ ህገ ወጥና ዘራፊ መሆኑን አንስተዋል። እየተካሄደ ያለው ህግን የማስከበር ሥራ በአጭር ጊዜ ተቋጭቶ ወንጀለኞች በህግ እንዲጠየቁና ሕዝቡ ሠላማዊ ኑሮውን እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።
የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥም ሆነ የከተማዋን ሠላም ለመጠበቅ በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውንም አስታውቀዋል።
የምክክር መድረኩ ዓላማ የህዝቦችን አንድነትና መተሳሰብ የበለጠ ለማጠናከር መሆኑንም የጎንደር ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሞላ መልካሙ አስታውቀዋል።
መንግሥት ህግን ለማስከበር በትህነግ ቡድን ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን በመረዳት የከተማዋን ሠላም ለማስጠበቅ በሚደረገው ጥረት ሁሉም ህዝቦች የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡም መድረኩ ጠቃሚ መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል። በውይይቱ በጎንደር ከተማ ከሚገኙ ክፍለ ከተሞች የተወጣጡ የትግራይ ተወላጆች ተሳታፊ ሆነዋል።
ዘጋቢ:- ኃይሉ ማሞ – ከጎንደር
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m