
ባሕር ዳር፡ ኅዳር 1/ 2013 ዓ.ም (አብመድ) የአማራና የትግራይ ህዝብ በወንድማማችነትና በመተሳሰብ ለዘመናት የኖሩ እንደሆኑ ያነሱት የትግራይ ተወላጆች በቆቦ ከተማ ለረጅም አመታት ትዳር መስርተው ሐብት አፍተው እየኖሩ መሆኑን ለአብመድ ተናግረዋል።
ሽፍታው የትህነግ ጁንታ በሐገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመው ጥቃት ቀድሞውንም ለህዝብና ለሐገር እንደማያስብ ያረጋገጠ ነው ብለዋል።
የትግራይ ህዝብ የከሐዲውን ቡድን እኩይ አላማ በማክሸፍ ህግና ስርዓትን ለማስከበር እየታገለ ካለው የሐገር መከላከያ ሰራዊት ጎን መሰለፍ አለባቸው ሲሉም በቆቦ ከተማ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች አሳስበዋል።
ህገወጡ ትህነግ እድሜያቸው ለውትድርና ያልደረሱ ህጻናት ጭምር ለጦርነት እያሰለፈ በመሆኑ የትግራይ ህዝብ ልጆቹን ከትህነግ እኩይ ድርጊት ሊታደጋቸው ይገባልም ብለዋል።
የትህነግን አፈናና እንግልት በመቃወምም ከአላማጣ ወረዳ ወደ ራያ ቆቦ ወረዳ የገቡ ነዋሪዎችም አሉ።
የማንነት ጥያቄያችን ይመለስ ብለን በተደጋጋሚ ስንጠይቅ ህገወጡ ትህነግ አፈና በማድረግ እያንገላታን በመሆኑና ከሰሞኑም በሀገር ላይ ክህደት በመፈጸሙ አካባቢውን ለቀን እንድንወጣ ምክንያት ሆኖናል ብለዋል።
ዘጋቢ፡- ስማቸው እሸቴ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m