
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 27/2013 ዓ.ም (አብመድ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በወቅታዊ የዲፕሎማሲ ስራዎች ዙሪያ መግለጫ ሰጧል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት መግለጫ ያለፉት ሳምንታት ስኬታማ የዲፕሎማሲ ስራዎች የተሰሩበት መሆኑን አንሰተዋል።
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር መካሄዱን ገልፀዋል።ከሶስቱም ሀገራት ሁለት ሁለት ባለሙያዎች ተመርጠው የመደራደሪያ አጀንዳዎችን ማቅረባቸውን አንስተዋል።በድርድሩ ላይ የአፍሪካ ህብረት ሚናውን እንዲጫወት አጀንዳ ቀርቦ ኢትዮጵያና ሱዳን መስማሰታቸውን ገልፀዋል። ሆኖም በግብፅ በኩል ተቀባይነት ስላላገኘ በቀጣይ ለድጋሜ ድርድር ይቀርባል ብለዋል።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ችግሮችን በአፍሪካዊ ማዕቀፍ የመፍታት ሀሳብን በመደገፍ የህብረቱ የአደራዳሪነት ሚና ማደግን መደገፏን አብራርተዋል።
ሀገሪቱ በገጠሟት ወቅታዊ ችግሮች ምክንያት ብሔራዊ ጥቅሟን የሚነካ ድርድር እንደማታካሂድም አስታውቀዋል።
የጎረቤት ሀገራት የኢትዮጵያን ሰላምና ደህንነት እንደሚደግፉ ገልፀውልናል ብለዋል።
ዘጋቢ፡- ዘመኑ ታደለ- ከአዲስ አበባ