
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 26/2013 ዓ.ም (አብመድ) “አንድ ነገር ከመናገራችን በፊት ስለምንናገረው ጉዳይ ማሰብ እና ማሰላሰል ያስፈልጋል። ኢትዮዽያ ትልቅ ሀገር ናት። ትልቅነት መመዘኛው ብዛትም ይሁን ሀብት ወይም ታሪክ በሁሉም ትልቅነቷን ታሟላለች። ከሁሉም በላይ ለራሱ ብቻ ሳይሆን ኢ-ፍትሀዊ እና ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶችን ሲያይ ለሌሎች የዓለም ሀገራትም ሳይቀር የብስና ውሀ አቋርጦም ለሌሎች መድህን ለመሆን የሚሞት ህዝብ ያላት ሀገር ነች::
ህዝቧ ልዩነቱንና ብዝሀነቱን እንደ ፀጋ የሚቆጥር ነው:: ይሁን እንጅ ስንዴ ውስጥ እንደሚበቅል እንክርዳድ ሁሉ ኢትዮጵያም ትህነግን አፈራች:: ይህ ቡድን ቢያንስ ቢያንስ በሰራው አፀያፊና አሳፋሪ ሀገርን በታማኝነት ያለመምራት ክህደትም ይሁን ሰውን እንደ ሰው ያለማክበር አረመኒያዊ ተግባር መፀፀትና ይቅርታ መጠየቅ ነበረበት:: ግን ዕድሉን መጠቀም ሲገባው የሌቦች፣ ዘራፊዎች፣ አጭበርባሪዎች እና ሌሎች ህገ ወጦች ሁሉ መድህን ነኝ ብሎ አወጀ::
ኢትዮዽያን በመራበት አሳፋሪ ብቃቱ ትግራይን ሊሞክር ዕድሉን አገኘ:: የልማት ሳይሆን የስድብ ቃላቶችን ሲያፈላልግ እና በአየር ላይ ሲረጭ ከርሞ ብንን ሲል ምንም የሰራው ተግባር የለም:: እናም ድሮ በምክንያት እና ጉልበቱ ሳይዝልና አንደበቱ ሳይደክም በበረሀ ያካበተውን ነፃ አውጭ ነኝ የትግል ዘዬ ትዝ አለው:: ሳያስብ መናገሩ አነሰበትና የኢትዮዽያ ህዝብ ኩራት: የአፍሪካ መድህን እና በዓለም የሚደነቀው የሀገር መከላከያ ሰራዊታችን ላይ ሳያልም ምላጭ ሳበ::
አሳዛኝ የቀብር ቦታውንም አዘጋጀ:: ውሏችን እጅግ ወርቃማ ነው:: ሰራዊታችን ምንጊዜም ያኮራል ነገም ድሉ ይቀጥላል:: የዚህ አሳፋሪ ቡድን መቋጫው እንደ እምባገነኖቹ እንደ እነ ስም አይጠሬ ይሆናል::”
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m