
ባሕር ዳር: ጥቅምት 27/ 2013 (አብመድ) የመቐለ፣ ሽሬ፣ አክሱም አና ሁመራ ኤርፖርቶች ለማንኛውም የበረራ አገልግሎት ዝግ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን አስታወቀ::
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ከዛሬ ጥቅምት 27/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ የመቐለ፣ ሽሬ፣ አክሱም አና ሁመራ ኤርፖርቶች ለማንኛውም የበረራ አገልግሎት ዝግ መሆናቸውን አስታወቀ።
ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ በተመሳሳይ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት (ኤርሜንስ) በተገቢው የመገናኛ ዘዴ (ኖታም) እንዲያውቁት መደረጉንም ፋብኮ ዘግቧል።