በጎንደር ከተማ አስተዳደር ‹‹ደማችን ለመከላከያ ሠራዊታችን›› በሚል መልዕክት የደም ልገሳ ፕሮግራም ዛሬ ተጀምሯል፡፡

505

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 26/2013 ዓ.ም (አብመድ) በጎንደር ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የደም ልገሳ ፕሮግራም በከተማ አስተዳደሩ በተዘጋጁ አራት ጣቢያዎች ነው፡፡ መርሃ ግብሩም ለሳምንት የሚቆይ ነው፡፡ ከደም ለጋሾች መካከል አንዱ የሆነው ጌትሽ አቡሃይ እንደተናገረው ደም መለገስ ሰብዓዊነት ቢሆንም ለሀገር ደኅንነት ሲባል ዳር ድንበርን እያስከበረ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና ልዩ ኃይል ሊደርስ የሚችለውን የደም እጦት ለመተካት ነው ብሏል፡፡ ከዚህ የበለጠ ዋጋ የሚያስከፍል ከሆነም ዝግጁ መሆኑን ወጣቱ ገልጧል፡፡

ወጣት አለማየሁ ታደሰ እንዳለው የዛሬ ደም መለገስ በቀጣይም ማንኛውንም ግዳጅ ለመቀበል ዝግጁነትን ለማሳየት መሆኑን ገልጿል፡፡ ሌሎች ደም ለጋሾችም ነገም የሀገርን ዳር ድንበር ለማስከበር ለሚደረገው ሃገራዊ ጥሪ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

እስከ ጥዋት በነበረው ጊዜ በአንድ ጣቢያ ብቻ 39 ዩኒት ደም ተሰብስቧል፡፡

ዘጋቢ፡- እመቤት ሁነኛው : ከጎንደር

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleአማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር የመሥራች ጉባኤውን በውክልና ለማካሄድ መወሰኑን አደራጅ ኮሚቴው ገለፀ።
Next articleሰበር ዜና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶክተር) የሰጡት መግለጫ