ከ25 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸዉ የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።

208

ጥቅምት 18/2013 ዓ.ም በተደረገ የኦፕሬሽን ሥራ በአፋር ክልል ዞን ሦስት ሀሩካ ወረዳ ብዙ ጊዜ በኮንትሮባንድ ክምችት የምትታወቀዉ ገዳማይቱ ከተማ በብዙ መጋዘኖች ዉስጥ ተከማችቶ የነበረ የኮንትባንድ ዕቃ መያዙ አስታውቋል፡፡

ግምታዊ ዋጋቸዉ ከ25 ነጥብ 9 ሚሊዮን የተገመተ የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል ሲጋራ ፣ ሺሻ፣ መድኃኒት ፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የፊት ቀለም ፣ አልባሳትና ልዩ ልዩ እቃዎች ይገኙበታል።

ጥቅምት 18 ቀን 2013 ዓ.ም ከጧቱ 12፡00 ላይ በጉምሩክ መረጃ ሠራተኞች ፣ በፌዴራል ፖሊስ እና በሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በጋራ በመሆን ተከማችቶ ባለበት ቦታ መያዝ ተችሏል ተብሏል፡፡
ምንጭ፡- ገቢዎች ሚኒስቴር

Previous articleየመከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ክልል ልዩ ሃይልና ሚሊሻ አባላት ስኬታማ ድል ማስመዝገባቸውን የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ ተናገሩ፡፡
Next articleህወሓት በመከላከያ ሰራዊት ላይ ባደረሰው ጥቃት በአካባቢው የተፈጠረው ውጥረት እንዳሳሰባቸው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ገለፁ፡፡