የመከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ክልል ልዩ ሃይልና ሚሊሻ አባላት ስኬታማ ድል ማስመዝገባቸውን የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ ተናገሩ፡፡

608

የክልሉ ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ በይፋዊ ገፃቸው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

<<እጅግ ስኬታማ ውሎ ነበረን፡፡ የክልላችን ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ እና የመከላከያ ሰራዊት በየደረጃው ያሉ ዓመራሮች እና አባላት በተቀናጀ መልኩ ያደረጉት ተጋድሎ ስኬታማ ነበር፡፡ በትናንትናው ዕለት በሶሮቃ እና ቅራቅር ከዕኩለ ሌሊት እስከ ረፋድ ተደጋጋሚ ማጥቃት ተሰንዝሮብን ነበር፡፡ ከረፋድ በኋላ በሰነዘርነው ማጥቃት በርካታ ቦታዎችን ተቆጣጥረናል፡፡ በተቆጣጠርናቸው ቦታዎች ያለው የህዝብ ድጋፍ ድንቅ ነበር፡፡ በርካታ ያለፍላጎቱ እንዲዋጋ የተገደደ የፀጥታ ኃይል በሰላም እጁን ሰጥቷል፡፡ እዋጋለሁ ብሎ የመረጠም ፊቱን አዙሮ እኛን ሲያግዝ ውሏል፡፡ ጦርነት አንፈልግም ስንል ጠላታችን ድህነት ነው ከሚል እንጅ ጦርነት ካለማወቅ አይደለም፡፡ ዛሬም በሌላ ድል ታጅቦ ያልፋል>> ብለዋል፡፡

Previous article“ሳንፈቅድ የተከፈተብንን የምንከላከለውን ጦርነት ዛሬ በሁሉም ግንባር ራሳችንን በመከላከል ተጨማሪ ቦታዎችና ንብረቶች እንዳይወሰዱ ማድረግ የሚያስችል ሥራ ተሠርቷል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ
Next articleከ25 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸዉ የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።