ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ

271

ዛሬ ጥቅምት 25/2013 ዓ. ም ከህወሃት የጥፋት ተልዕኮ ተቀብለው በጋምቤላ ክልል ብሄር ብሄረሰቦችን ለማጋጨት አሲረው ሲንቀሳቀሱ ነበር በሚል የተጠረጠሩ ጸጋዬ መብርሃቱ (ካህሳይ)፣ ገብረ ማሪያም አናንያ፣ ዋስትና ተሾመ (ጃልሴና)፣ አብርሃም መሃሪ፣ ኮሎኔል ተስፋዬ (ባሌስትራ) እና ሌሎች 19 የህወሃትና የኦነግ ሸኔ የጥፋት ኃይሎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በክልሉ ብሄር ብሄረሰቦችን በማጋጨት አካባቢውን የትርምስ ቀጠና ለማድረግ አሲረውት የነበረው ሴራ ከሽፏል፤ ግለሰቦቹም በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በተመሳሳይ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን ተፈጽሞ የነበረ ተመሳሳይ ጥፋት በዚያው በክልሉ ውስጥ በአሶሳና ካማሼ ዞኖች ብሔር ብሄረሰቦችን በማጋጨት አካባቢውን የትርምስ ቀጠና በማድረግ እልቂት ለመፈጸም የህወሃት የጥፋት ቡድን አባል ከሆነው አባይ ጸሃዬ ተልዕኮ ወስደው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ዮሃንስ ግርማይና ርዕሶም ግርማይ ከሌሎች 20 ግብረ አበሮቻቸው ጋር በቁጥር ስር ውለዋል፡፡

በጋምቤላና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች እነዚህን የጥፋት ሃይሎች በቁጥጥር ስር ለማዋልና ሴራቸውን ለማክሸፍ በተፈጸመ ኦፕሬሽን የብሄራዊ መረጃ ደኀንነት አገልግሎት፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን እንዲሁም የየክልሎቹ የጸጥታ አካላት በቅንጅት ተሳትፈዋል።

በሌሎች ክልሎችም ተመሳሳይ ጥፋት ለመፈጸም ተልዕኮ ወስደው ሲንቀሳቀሱ በነበሩ የጥፋት ሃይሎች ላይ ጥብቅ ክትትል እየተደረገ ነው።
ፋብኮ እንደዘገበው አጠቃላይ የጥፋት ሴራውን በማክሸፍ ዙሪያ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በተመለከተ በተከታታይ መረጃዎችን ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታውቋል።

Previous article“ሰራዊቱ በሰፈረባቸዉ ካምፖች የተከፈተበትን የከሃዲዎች ጥቃት በብቃት መክቶ ወደ ማጥቃት እርምጃ ተሸጋግሯል” መከላከያ ሚኒስቴር
Next article“ሳንፈቅድ የተከፈተብንን የምንከላከለውን ጦርነት ዛሬ በሁሉም ግንባር ራሳችንን በመከላከል ተጨማሪ ቦታዎችና ንብረቶች እንዳይወሰዱ ማድረግ የሚያስችል ሥራ ተሠርቷል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ