“ሰራዊቱ በሰፈረባቸዉ ካምፖች የተከፈተበትን የከሃዲዎች ጥቃት በብቃት መክቶ ወደ ማጥቃት እርምጃ ተሸጋግሯል” መከላከያ ሚኒስቴር

271

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 25/2013 ዓ.ም (አብመድ) ሰራዊቱ በሰፈረባቸዉ ካምፖች የተከፈተበትን የከሃዲዎች ጥቃት በብቃት መክቶ ወደ ጸረ ማጥቃት እርምጃ መሸጋገሩን የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ። ሰራዊቱ ተኩስ በተከፈተበት ካምፖች ሁሉ በጠንካራ መከላከል ውጊያ የከሃዲውን ሃይል በጀግንነት መክቶ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰበት ይገኛል፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊትና የአማራ የጸጥታ ሃይል ተቀናጅተዉ በሰሜን ጎንደር ዞን ቀራቅር በተባለ ቦታ የእብሪተኛዉ ቡድን የሰነዘረዉን የማጥቃት ውጊያ በብቃት በመመከት በዚህ ሃይል ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳቁሳዊ ኪሳራ አድርሶበታል፡፡

ሰራዊቱ በዛሬዉ እለት ከሰዓት በኋላ በወሰደዉ ቅንጅታዊ የማጥቃት እርምጃ ከቀራቅር በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘዉ ከፍተኛ ቦታ ላይ የነበረዉን የእብሪተኛዉ አጥፊ ቡድን ሃይል በከፍተኛ ሁኔታ በማጥቃት ቦታዉን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታውቋል።

ኢዜአ እንደዘገበው ጀግናዉ ሰራዊት በወሰደዉ የማጥቃት እርምጃ በዚህ ነብሰ በላ ቡድን ሃይል ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊ ኪሳራ በማድረስ የቡድንና የነብስ ወከፍ መሳሪያዎችንም ማርኳል ብሏል መከላከያ ሚኒስቴር በመግለጫው፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleበተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በአማራ ህዝብ ላይ ጥቃት በሚፈጽሙ አካላት ላይ ድርጊታቸውን የሚመጥን እርምጃ መንግስት አለመውሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪወች ተናገሩ፤ መንግስት ሕግ የማስከበርና የሕዝብን ደኅንነት የመጠበቅ ኃላፊነቱን መወጣት ይገባዋልም ብለዋል፡፡
Next articleከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ