ብሔርን ተኮር ያደረገ ጥቃት ሊቆም እንደሚገባ አስተየታቸውን የሰጡ የደባርቅ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

318

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም (አብመድ) በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ በደረሰው ጥቃት ማዘናቸዉን ለአማራ ብዙሐን መገናኛ ድርጅት አስተያየታቸዉን የሰጡ የደባርቅ ከተማ ነዋሪዎች ገልጸዋል። ጥቃቱ ብሔር ተኮር በመሆኑ አንድነታችንን በመሸርሸር ሀገሪቱ እንድትከፋፈል የሚፈልጉ አካላት የሚፈፅሙት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የአማራ ሕዝብ የዋህና ከማንኛዉም የማኅበረሰብ ክፍል ጋር በጋራ የኖረ ሕዘብ መሆኑን ያነሱት አስተያየት ሰጭዎቹ አማራ ኢትዮጵያዊ አስተሳሰቡን ይዞ በመቀጠል በአማራነቱ ደግሞ በመኩራትና ራሱን ተደራጂቶ መከላከል ይገባዋል ብለዋል።

ተግባሩ አሳዛኝና አረመኒያዊ ተግባር መሆኑንም የደባርቅ ከተማ ነዋሪ ዋና ሳጅን ካሳዬ ቢሹ ገልጸዋል፡፡ ሌላኛዉ አስተያዬት ሰጪ አቶ አበበ ተሾመ ብሔርን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን መንግሥት ሊያስቆም ይገባል፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ድርጊቱን ሊያወግዘውም እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ መንግሥት መግለጫዎችን በተደጋጋሚ ቢያወጣም የአማራ ሕዝብን ሊታደገው ስላልቻለ ወደ ሕጋዊ ርምጃ መግባት አለበት ብለዋል አቶ አበበ፡፡

አማራ ብዙ ግፍና ጭቆና እየደረሰበት ያለና በቀጣይም የግፉ መቆሚያ የማይታወቅበት መሆኑን የገለጹት ወይዘሪት ዝማም አቡሃይ በበኩላቸው ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸውና አሁንም የአማራ ሕዝብ ከእንደዚህ አይነት ጥቃቶች ራሱን ለመከላከል ወደ አንድ ሊመጣ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

አስተያየት ሰጭዎቹ መንግሥት መግለጫዎችን ከማዉጣት ባለፈ ጥቃት አድራሾች ላይ ሕጋዊ እርምጃ ሊወስድ እንደሚገባ፤ አማራዉን መሰረት ያደረገን ጥቃትና በየጊዜዉ እየደረሰበት ያለውን መፈናቀል ሊያስቆም ይገባል ነው ያሉት፡፡ የአማራ ሕዝብ ተደራጅቶ ራሱን መጠበቅ እንዳለበትም ተናግረዋል፡፡

ዘጋቢ፦ ደስታ ካሳ፡ ከደባርቅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article“መንግስት እውነተኛ የህግ ተጠያቂነትን ሊያሰፍን ይገባል” የሕግ ምሁራን
Next articleበተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በአማራ ህዝብ ላይ ጥቃት በሚፈጽሙ አካላት ላይ ድርጊታቸውን የሚመጥን እርምጃ መንግስት አለመውሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪወች ተናገሩ፤ መንግስት ሕግ የማስከበርና የሕዝብን ደኅንነት የመጠበቅ ኃላፊነቱን መወጣት ይገባዋልም ብለዋል፡፡