የመግለጫ ጋጋታ ህዝብን ከሞት አያድንምና መንግስት በአማራ ህዝብ ላይ እየተደረገ ያለዉን ጭፍጨፋ ማብራሪያ እንዲሰጥበት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጠየቁ፡፡

360

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም (አብመድ) በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ ጥቃት አድርሰዋል የተባሉት ኦነግ ሸኔ እና ህወሃት በሽብርተኝነት እንዲጠየቁ የምክር ቤቱ አባላት አሳስበዋል፡፡

ብልጽግና ያለሰዉ ምንም ባለመሆኑ ህይወቱ እያለፈ ያለን ህዝብ ድምጽ መወከል አንችልም ሲሉ እንደራሴወቹ ገልፀዋል፡፡

ኢትጵያ በአንድ ዘር የምትገነባ ባለመሆኗ ሁሉንም መጠበቅ ሃላፊነት የመንግስት ነዉ፤ ይህንን ሃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት ባለመቻሉ በንጹሃን ዜጎች ላይ ጭፍጨፋ እየደረሰ ነዉ ብለዋል፡፡

በመንግስት መግለጫ ላይም ብሄሩን ላለመጥቀስ የሚደረግ ማሽሞንሞን ተገቢ ባለመሆኑ የተጨፈጨፈዉ አማራ ነዉ በሚል መስተካከል እንደሚኖርበት የምክር ቤቱ አባላት አንስተዋል፡፡

ሀገሪቱ እንድትፈርስና እንድትበጣበጥ ይፈልጋሉ የሚባሉት ሃይሎች ባንክ ሲዘርፉ ዝም በመባላቸዉ ሃይል አጠናክረዋል፤ ህገወጥ ቡድኑ ከህጋዊዉ መንግስት በላይ ባለመሆኑ መንግስት የህዝብ ከለላነቱን እንዲያረጋግጥ ጠይቀዋል፡፡

በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ የመከላከያ ሰራዊት በቦታዉ ሲነሳ በምትኩ ሌላ የፀጥታ ሃይል መተካት የነበረበት ቢሆንም ይህ ባለመሆኑ የአሠራር ክፍተት ብቻ ተብሎ መታለፍ የለበትም ብለዋል እንደራሴዎቹ፡፡

ዘጋቢ፡- ጽዮን አበበ- ከአዲስ አበባ

Previous articleበምዕራብ ወለጋ ጉሊሶ ወረዳ በአማራዎች ላይ በተፈፀመው ጥቃት መንግስት ተጠያቂ ነው ሲል የአማራ ምሁራን መማክርት ገለጸ።
Next articleበምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ ዋጋ ቃንቃ ቀበሌ በንፁሀን ዜጐች ላይ በደረሰው አሰቃቂ ጥቃት የፌዴሬሽን ምክር ቤት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገልጿል፡፡