
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም (አብመድ) የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ የ2013 በጀት ዓመት የፖለቲካ፣ የልማትና መልካም አስተዳደር ሥራዎች ዕቅድ ትውውቅ በባሕር ዳር ከተማ ማካሄድ ጀምሯል።
ለሦስት ቀናት በሚቆየው የዕቅድ ትውውቅ መድረክ የክልል፣ የዞንና የወረዳ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡
የፖለቲካና ድርጅት ስራዎች መሪ ዕቅድ ውይይቱን ከመጀመሩ በፊትም በተለያዩ አካባቢዎች በግፍ ለተገደሉ አማራዎች የህሊና ጸሎት ተደርጓል።