”ሰላማዊ ሕዝብን በመጨፍጨፍና በማስጨፍጨፍ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች ሰው የመሆን ስብዕና የጎደላቸው ናቸው” አቶ ኡሞድ ኡጁሉ

234

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም (አብመድ) “ሰላማዊ ሕዝብን በመጨፍጨፍና በማስጨፍጨፍ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች ሰው የመሆን ስብዕና የጎደላቸው ናቸው” ሲሉ የጋምቤላ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ ተናገሩ።

ርእሰ መሥተዳድሩ በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈፀመውን ጥቃት በማውገዝ የተሰማቸውን ሃዘንም ገልፀዋል፡፡ ጥቃቱን ባደረሱ አካላት ላይ መንግሥት የማያዳግም እርምጃ ሊወስድ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

‘’በዜጎች ላይ የደረሰው አሰቃቂ ጥቃት እጅጉን የሚያሳዝንና ከሰብዓዊነት ያፈነገጠ ነው” ብለዋል ርእሰ መሥተዳድር፡፡ ጥቃቱ ፍፁም ሰላማዊ በሆኑ ንፁሃን ዜጎች ላይ የተቃጣ መሆኑ አጥፊ ቡድኑ የሚከተለው መንገድ ኋላቀርና ጭካኔ የተሞላበት መሆኑን እንደሚያመላክት ጠቅሰዋል።

“ሰላማዊ ሕዝብን በመጨፍጨፍና በማስጨፍጨፍ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች ሰው የመሆን ስብዕና የጎደላቸው ናቸው” ብለዋል። ቡድኖቹ የፈጸሙት አፀያፊ ድርጊት የኢትዮጵያውያንን አንድነትና ወንድማማችነት ሊቀይረው እንደማይችል ተናግረዋል፡፡

ኢዜአ እንደዘገበው የጥፋት ሀይሎችን በጋራ በመዋጋት አገሪቱ የዜጎች ደኅንነት የተረጋገጠባት እንድትሆን ሁሉም በቁርጠኝነት መስራት እንደሚጠበቅበት ርእሰ መሥተዳድሩ ኡሞድ ኡጁሉ አሳስበዋል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleበምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ ዋጋ ቃንቃ ቀበሌ በንፁሀን ዜጐች ላይ በደረሰው አሰቃቂ ጥቃት የፌዴሬሽን ምክር ቤት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገልጿል፡፡
Next articleየአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ የ2013 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ እያካሄደ ነው።