
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም (አብመድ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት እንደገለጸው በንፁሀን ዜጐች ላይ እየደረሰ ያለው አሰቃቂ ጥቃት በተደጋጋሚ እየተፈፀመ የዜጐችን ህይወት እየቀጠፈም ይገኛል፤ በመሆኑም ለሀገርና ለሰው ልጅ ክብርና ስብዕና በሌላቸው የጥፋት ሃይሎች ላይ መንግስት የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ አለብት ብሏል፡፡
የሃገሪቱ ብሄሮች ፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች መንግስት በነዚህ የጥፋት ኃይሎችና አሸባሪዎች ላይ ለሚወስደው እርምጃ ከመንግስት ጐን በመቆም አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ነው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጥሪውን ያቀረበው፡፡
ምክር ቤቱ ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን የገለፀ ሲሆን ለተጎጂ ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች እንዲሁም ለመላው ኢትዮጵያውያን መጽናናትን እንደሚመኝ ገልጿል፡፡