
“አማራዊ ማንነታችን የጥቃት ምንጭ መሆኑ ሊቆም ይገባል” ሲሉ የንግድ ሚኒስትሩ አሳሰቡ፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 23 /2013 ዓ.ም (አብመድ) የንግድ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል በወለጋ የደረሰውን ጥቃት አስመልክቶ በቲውተር ገፃቸው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው “ ከወንድም ህዝቦች ጋር በአንድነት ስጋና ደም ገብረን ባቆምናት ኢትዮጵያ አማራዊ ማንነታችን የጥቃት ምንጭ መሆኑ ሊቆም ይገባል፤ መከራ ያጠነክረናል እንጂ አያጠፋንም፤ ኢትዮጵያም ትቀጥላለች” ብለዋል፡፡
ሚኒስትሩ እንዳሉት “ሁሉም ትውልድ የራሱ የቤት ስራ አለበት፤ በመስዋዕትነታችን ከሌሎች ወንድም ህዝቦች ጋር በነጻነት፣ በእኩልነት እና በፍትሃዊ ተጠቃሚነት የምንስተናግድባት ኢትዮጵያን እናፀናለን ” ነው ያሉት፡፡