
ባሕርዳር፡ ጥቅምት 13/2013 ዓ.ም (አብመድ) የ2012 ትምሕርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ ከጥቅምት 16 እስከ 30 /2013 ዓ.ም በየትምሕርት ቤቶቹ እንደሚካሄድ የትምሕርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ እንደሚያመላክተው የፈተና ምዝገባ ሂደቱን በተቀላጠፈ ሁኔታ ለማካሄድ በተዘጋጀው ሶፈትዌር “Enrollment Kit” ላይ ምዝገባ ለሚያከናውኑ የአይ .ሲ .ቲ ባለሙያዎችና የፈተና ክፍል አስተባባሪዎች በየክልል ከተሞች የግንዛቤ ማስጨበጫ መሰጠቱ ተመልክቷል።
የ2012 ትምሕርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በኦላይን እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4