በከተሞች የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፣ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፡፡

262

ባሕርዳር፡ ጥቅምት 13/2013 ዓ.ም (አብመድ) በከተሞች ለሰላም እጦት መንስኤ የሆኑ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አስታወቁ፡፡
ፕሬዝዳንቷ ይህን ያስታዎቁት በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ባለው የከተሞች የሰላም ፎረም ላይ ነው፡፡ “የፍትህና ተጠያቂነት መጓደልና ስራ አጥነት በከተሞች የሚስተዋሉ ዋና ዋና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ናቸው” ብለዋል፡፡

ችግሮቹን ለመፍታት ከህዝቡ ጋር በግልጽ ውይይት መደረግ እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡ የከተሞች ሠላም ለሀገራችን ዘላቂ ልማት ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ በፖሊሲ ሊደገፍ እንደሚገባ አስታውቀዋል።

ኢዜአ እንደዘገበው የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ያዘጋጀውና “ከተሞችና ሰላም” በሚል መሪ ቃል በአርባምንጭ እየተካሄደ ባለው የከተሞች ፎረም ላይ ሚኒስትሮች፣ የክልል የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽ ቢሮ ኃላፊዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው።
በፎረሙ ላይ “የከተሞች ሰላም ለሀገር ኢኮኖሚ ያለው አስተዋጽኦ” በሚል ርዕስ ሰነድ ቀርቦ ውይይትይደረግበታል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4

Previous articleየጥሬ ቆዳና ሌጦ ምርትን ከብክነት ለመታደግ እየሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ገለጸ፡፡
Next article756 የምግብ አይነቶችን መዝግቦ ለኅብረተሰቡ መረጃ ማቅረቡን የኢትዮጵያ የምግብና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡