የአንበጣ መንጋና የጎርፍ አደጋ ያስከተሉትን የምርት መቀነስ በመስኖ እርሻ ለማካካስ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡

182

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 13/2013 (አብመድ) በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የአትክልትና ፍራፍሬ ዳይሬክቶሬት የአትክልት ባለሙያ ተፈራ ሰይፉ እንደተናገሩት በ2013 ዓ.ም የመስኖ እርሻ 248 ሺህ ሄክታር ማሳ በዘር ይሸፈናል፡፡ በመስኖ እርሻ ልማት 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን አርሶ አደሮች በመሳተፍ 37 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማገኘት እቅድ እንደተያዘም ነው የተናገሩት፡፡ አርሶ አደሮች ገበያ ተኮር ሰብሎች ላይ ትኩረት በማድርግ የመስኖ ስራቸውን እንዲያከናውኑ አቅጣጫ ተይዟል ያሉት አቶ ተፈራ 80 በመቶ የሚሆን ማሳ በአተክልትና ፍራፍሬ እንደሚሸፈን አስረድተዋል፡፡

በቆላማ አካባቢዎች ላይም የቆላ ስንዴ ለመዝራት ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል፤ ለመስኖ እርሻ በቂ ግባት መኖሩንም አቶ ተፈራ አርጋግጠዋል፡፡ እየተደረገ ያለው ቅድመ ዝግጅት በአንበጣ መንጋና በጎርፍ አደጋ የወደመውን ሰብል ማካካስ የሚያስችል እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

በቅድመ ዝግጅቱ ለመስኖ ልማት የሚውሉ በመንገድ ሥራና በጎርፍ ጉዳት የደረሰባቸውን ቦዮች መጠገንና የመጥረግ ሥራም እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ የክረምቱ ጎርፍ ከፍተኛ ስለ ነበር በርካታ ቦዮች በደለል መሙላታቸውን አቶ ተፈራ ተናግረዋል፡፡ በአርሶ አደሮች የሚጠገኑና ከአርሶ አደሮች አቅም በላይ የሆኑ የመስኖ ቦዮችም መለየታቸውን ጠቁመዋል፡፡

ዘጋቢ፡- አዳሙ ሽባባው

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት አሰጣጥና ተደራሽነት ችግሮች እንዲስተካከሉላቸው የምዕራብ ጎንደር ዞን ነዋሪዎች ጠየቁ።
Next articleተቀላቅለው ሲሸጡ የነበሩ የምግብ ዘይቶች በቁጥጥር ስር ዋሉ።