የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት አሰጣጥና ተደራሽነት ችግሮች እንዲስተካከሉላቸው የምዕራብ ጎንደር ዞን ነዋሪዎች ጠየቁ።

705

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 13/2013 (አብመድ) በምዕራብ ጎንደር ዞን ከሚገኙ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ ነዋሪዎች ከመብራት ኃይል አገልግሎት አሰጣጥና ተደራሽነት ጋር በተያያዘ ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱ በዞኑ ውስጥ በሚገኙ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የሚስተዋሉ የመብራት አገልግሎት አሰጣጥና የማስፋፊያ ክፍተቶች ተነስተዋል።

ነዋሪዎቹ የመብራት ተደራሽነት ችግር ፣ የተዘረጉ የኤሌክትሪክ መስመሮች አገልግሎት አለመስጠት፣ የኤሌክትሪክ ቆጣሪን በወቅቱ አለማየትና የቆጣሪ አገልግሎት ክፍያ መጋነን ክፍተቶች እንዲስተካከሉ ጠይቀዋል።

በተዘረጉ የኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ ጉዳት ሲደርስ ፈጥኖ ምላሽ ያለመስጠት ችግር እንዳለም በውይይቱ ተነስቷል።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የጎንደር ዲስትሪክት ዋና ዳይሬክተር ሞገስ አበራ የተነሱ ጥያቄዎች ትክክል መሆናቸውን አምነው በቀጣይ ችግሮችን ለማስተካከል እንደሚሰራ ለውይይቱ ተሳታፊዎች ተናግረዋል።

የማህበር ቤቶችና መብራት ያልደረሰባቸው አካባቢዎች ከመብራት ኃይል ጋር በመነጋገር ግምት በማሰራትነና ክፍያ በወቅቱ በመፈጸም የመብራት ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉም ገልፀዋል ።

የመብራት ምሰሶ የማያስፈልጋቸውና መስመር ላይ የሚገኙ መብራት ፈላጊዎች ደግሞ ያገልግሎት ክፍያ በመክፈል መብራት ማግኘት እንደሚችሉም አቶ ሞገስ ተናግረዋል ።

በ2013 ዓ.ም የመብራት አገልግሎትን በዞኑ ተደራሽ ለማድረግ ለከተማ አስተዳደሮችና ወረዳዎች እቅድ መያዙንም አቶ ሞገስ ገልጸዋል።

ኅብረተሰቡ ውዝፍ ክፍያን በመክፈልና በየቦታው የሚሰረቁ የመብራት ሃይል ንብረቶች የራሱ መገልገያ እንደሆኑ ተረድቶ መጠበቅ እንደሚገባውም አስገንዝበዋል።

ዘጋቢ፡- ዳንኤል ወርቄ: ከገንዳውሃ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleአደጋን ቀድሞ ለመከላከል የሚያስችል የ220 ሚሊዮን ብር በላይ ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ።
Next articleየአንበጣ መንጋና የጎርፍ አደጋ ያስከተሉትን የምርት መቀነስ በመስኖ እርሻ ለማካካስ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡