
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 12/2013 (አብመድ) በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ በጋራ የሚካሄዱ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ተቋርጠው መቆየታቸው ይታወሳል፡፡
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከመከሰቱ በፊት በጋራ የሚካሄደው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አንደኛ ዙር አዘጋጅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሆኑ አይዘነጋም፤ በዚህ ወቅት እንደ ሀገር ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚረዱ ጥንቃቄዎች እየተተገበሩ በጋራ ወደሚካሄደው አካል ብቃት እንቅስቃሴ መመለስ እንደሚቻል ተነግሯል፡፡ ይህን ተከትሎም ከህዳር 6/2013 ዓ.ም ጀምሮ ሰፋ ያለውን ማኅበረሰብ የሚያሳትፈው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች እንደሚጀመር የአማራ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አዱኛ ይግዛው አስታውቀዋል፡፡
በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ሁለተኛው ዙር የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መክፈቻ ስነ ስርዓት በክልሉ እንደሚካሄድም ጠቁመዋል፡፡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴው በቀጣይነት እንዲካሄድ ይሠራልም ብለዋል ምክትል ኮሚሽነሩ፡፡
አካል ብቃት እንቅስቃሴው የሚካሄድባቸው ቦታዎች እንደሚመረጡም አቶ አዱኛ ጠቁመዋል፡፡
በየአካባቢው የተደራጁ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማኅበራት፣ የአካል ብቃት ባለሙያዎች ማኅበር፣ አሰልጣኞችን እና የሰውነት ማጎልመሻ መምህራን ሰብስቦ በማማከርና ቅስቀሳ በማድረግ በአካል ብቃት እንቅስቃሴው የሚሳተፉ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች የራሳቸውን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንዲጠቀሙ እንደሚደረግ አቶ አዱኛ አስታዉቀዋል፡፡
የአካል ብቃት እንቅስቃሴው በሽታ መከላከልን ዋናው ዓላማ ያደረገ ሲሆን በዕለቱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የክልሉ ስፖርት ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
ዘጋቢ፡- ኪሩቤል ተሾመ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
