የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን በሥስት ዓመት ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ፡፡

373

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 12/2013 (አብመድ) 2 ሺህ 160 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ግድብ በሥስት ዓመት ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ (
አስታውቀዋል።

የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ እንዳሉት በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ2025ዓ.ም በአገር አቀፍ ደረጃ ለሚገነባው ኢኮኖሚ 20 ሺህ ሜጋ ዋት ኃይል እንደሚያስፈልገው በስትራቴጂክ ዕቅድ ተቀምጧል። በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽ ለማድረግ ዕቅድም ተይዟል፤ ከዚህ አንጻር የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን በሶስት ዓመት ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑን አስታውቀዋል።

ግድቡ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኘውን የጊቤ ሦስት ውሃ የሚጠቀም በመሆኑ 6 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሊትር ውኃ ብቻ እንዲይዝ ተደርጎ እንደሚገነባና ይህም ግድቡን በፍጥነት ለማጠናቀቅ ዕድል ይሰጣል ነው ያሉት።

ግድቡ “በገበታ ለሀገር” የኮይሻ ፕሮጀክት መካተቱን ጠቅሰው፤ የግድቡ በፍጥነት መጠናቀቅ አካባቢውን የጎብኝዎች መዳረሻ በማድረግም ሚናው ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

የፕሮጀክቱ የኮንትራት ስራዎች ተቆጣጣሪ እዩኤል ሰለሞን እንደተናገሩት በእስካሁን ሂደት የውኃውን ተፈጥሯዊ አቅጣጫ ማስቀየርን ጨምሮ መሠረታዊ የቁፋሮ ሥራዎች ተጠናቀዋል፤ የማስተንፈሻ ግንባታ ቁፋሮው ከግማሽ በላይ መከናወኑንም አክለዋል። ።

ዋናው ግድብና የኃይል ማመንጫው በተለያዩ ቦታዎች መኖራቸው አንደኛው ግንባታ ሌላኛውን ሳይጠብቅ በተመሳሳይ ጊዜ እንዲከናወኑ ዕድል ይሰጣል ብለዋል።

የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በጊቤ-ኦሞ ወንዝ ቀጣና ከሚገኙ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች አራተኛው ነው።

ለአራት ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል የፈጠረው የኮይሻ ኃይል ማመንጫ የግንባታ ስምምነቱ የተፈረመው በመጋቢት 2008 ዓ.ም ነው።

ኢዜአ እንደዘገበው የፕሮጀክቱ አሁናዊ የግንባታ አፈፃፀም 39 በመቶ ደርሷል።

የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ግድብ በኢትዮጵያ ከሕዳሴ ግድብ ቀጥሎ ሁለተኛው ግዙፍ ፕሮጀክት ነው።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleበኢትዮጵያ እየተስተዋለ ያለውን ግጭት ለማስወገድ በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አሳሰበ፡፡
Next articleበኢትዮጵያ በየወሩ በጋራ ሲካሄድ የቆየው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በአማራ ክልል ህዳር 6/ 2013 ዓ.ም ዳግም ሊጀመር ነው፡፡