
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 12/2013 (አብመድ) በኢትዮጵያ የሚታየውን ግጭት እና አለመረጋጋት ለማስወገድ የሃይማኖት መሪዎች፣ መንግሥት እና ምዕመናን ትኩረት ሰጥተው ሊሠሩ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አሳስቧል፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የቅዱስ ሲኖዶሱን ጉባኤ ሲከፍቱ እንዳሉት በኢትዮጵያ እየተስተዋሉ ያሉት ግጭቶችና አለመግባባቶች ብዙ ጉዳቶችን እያስከተሉ ነው፡፡
ልዩነቶችን በውይይት በመፍታት እርቅን ማስፈን እና ዘላቂ ሰላምን ማረጋገጥ እንደሚገባ ፓትርያርኩ አሳስበዋል፡፡
ቤተ ክርስቲያኗ የአክራሪዎች፣ የተቃራኒዎች እንቅስቃሴ እንዲሁም ውስጣዊ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እየገጠሟት መሆኑን ተናግረው ጉባኤው እነዚህን ችግሮች ለመፍታት በንቃት እንዲሠራ አቡነ ማትያስ ማሳሰባቸውን ኢብኮ ዘግቧል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
