የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አጭር የጽሁፍ መልዕክት የገቢ ማሰባሰቢያ 3ኛ ዙር ሁለተኛ ተሸላሚ መኪናቸውን ተረክበዋል፡፡

199

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 12/2013 (አብመድ) ወይዘሮ አሰፋሽ አፈወርቅ ይባላሉ፤ ነዋሪነታቸው ደግሞ ኢሉባቡር በቾ ወረዳ ነው፡፡ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አጭር የጽሁፍ መልዕክት ገቢ ማሰባሰቢያ የሽልማት መርሃግብር ዘመናዊ ቢዋይ ዲ መኪና ተረክበዋል።

የስልክ መልዕክት የገቢ ማሰባሰቢያው የተጀመረው ባሳለፍነው አመት የካቲት ወር ላይ ነው፤ በዚህም ከ67 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉ ተጠቅሷል።

የቀድሞ የምድር ጦር ሰራዊት አባላትና የሲቪል ሰራተኞች ማህበር የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ አባላት በርክክብ ሥነስርዓቱ ላይ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል የ10 ሺህ ብር ስጦታ አበርክተዋል።

ስጦታውን ያስረከቡት የቀድሞ የምድር ጦር ሰራዊት አባላት ድጋፋቸው ቀጣይ እንደሚሆንና ሁሉም ባለው አቅም ለህዳሴ ግድብ አሻራውን እንዲያኖር ጥሪ አቅርበዋል።

የግድቡ የመጀመሪያው የውሃ ሙሌት ከተካሄደ በኋላ የህዝቡ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉም ተገልጿል።

እንደ ፋብኮ ዘገባ በመስከረም ወር ብቻም ከ197 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉና ይህም ከእስካሁኑ ከፍተኛ መሆኑ ተጠቁሟል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article‘‘የትምሕርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል የሚጠበቅብኝን ሁሉ አደርጋለሁ፡፡’’ ባለሃብት አቶ ተመስገን
Next articleበኢትዮጵያ እየተስተዋለ ያለውን ግጭት ለማስወገድ በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አሳሰበ፡፡