
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 11/2013 (አብመድ) ባለፉት ሁለት ዓመታት በመንግስትና በምክር ቤቱ ተሰሩ ያሏቸዉን ሥራዎችና ተግዳሮቶች የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤዉ አንስተዋል።
በደንምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ የታገቱ ተማሪዎችና የዘገዩ የፍትህ ጉዳዮችን በተመለከተ አብመድ ለአፈ ጉባኤው ጥያቄ እንስቷል፤ ተማሪዎንችን ማገት አለመረጋጋት እንዲፈጠር ለማድረግ ቢሆንም ምክር ቤቱና የፍትህ አካላት በቅርበት እየተከታተሉት እንደሆነ ምላሽ ሰጥተዋል አፈጉባኤዉ።
“የዘገየ ፍትህ እንዳልተፈጸመ ይቆጠራል” እንዲሉ በደምቢ ዶሎ አካባቢ የታገቱ ተማሪዎች አንድ ዓመት ገደማ ሆኗቸዋል። ይሁን እንጂ ምክር ቤቱ አሁንም ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ እንደሆነም ጠቅሰዋል፤ የፍትህ አካላትም አስፈላጊዉን ሁሉ እያደረጉ እንደሆነ ተናግረዋል።
እንደ አፈ ጉባኤው መግለጫ ለውጡ ያመጣቸው የሰብአዊ መብት፣ ዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ፣ የመገናኛ ብዙኃን ነጻነት ፣ የተለያዩ አዋጆች መሻሻልና እንደ አዲስ መዉጣት ተጠቅሰዋል፤ የፋይናንስ ስርዓት፣ የግብርና መካናይዜሽን፣ የተለያዩ ኮሚሽኞች መቋቋም፣ የዉጭ ግንኙነትና ደህንነት ፖሊሲ እና ዜጋ ተኮር መሆን በለዉጡ የተመዘገቡ መሆናቸውን አፈ ጉባኤው ጠቅሰዋል።
ይሁን እንጂ ተግዳሮት በመኖራቸው የሀገርን አንድነት ለመናድ የሚሰሩ አካላት ከድርጊታቸዉ እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።
በሀገሪቱ ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል እንዲኖርና የሚወሰኑ የመሬት አስተዳደር ቅሬታዎችን ለመፍታት አሰራሩ መዘመን እንዳለበት አፈ ጉባኤው በፋይናንስ አስተዳደር በኩልም አሰራርን መቃኘት እንደሚያሥፈልግ አሳስበዋል።
ዘጋቢ:-ፅዮን አበበ- ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
