የፌዴሬሽን ምክር ቤት 15ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን አከባበር ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየመከረ ነው፡፡

355

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 11/2013 (አብመድ) የዘንድሮው የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን ከወትሮው በተለየ ከልዩነት ይልቅ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን በሚያጠናክር አግባብ እንደሚከበር የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አደም ፋራህ ተናገሩ።

ምክር ቤቱ 15ኛውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን አከባበር የባለድርሻ አካላት ሚናን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር በአዳማ እየመከረ መሆኑን አስታውቋል።

አፈ ጉባኤ አዳም ፋራህ የምክክር መድረኩን በንግግር ሲከፍቱ እንደተናገሩት የዘንድሮውን በዓል የሕዝቦችን ወዳጅነት እና ዴሞክራሲያዊ አንድነትን በሚያጠናክሩ ተግባራት ለማክበር የተለያዩ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን ተናገረዋል።

የዘንድሮው የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የአከባበር ለውጥ የተደረገበት መሆኑ ተመላክቷል። በተለያዩ ማኅበራዊ አገልግሎትና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙትና ትስስርን በሚያጠናከሩ መርሀሃግብሮች ለማክበር የተለያዩ ስልቶች መቀየሱን መግለጹ የሚታወስ ነው።

ምንጭ፦ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ማኅበራዊ ገጽ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ (ዶክተር) የማክሮ-ኢኮኖሚ ኮሚቴ ጋር ተወያዩ።
Next articleየኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዲስ መልክ ሊደራጅ ነው።