የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዲስ መልክ ሊደራጅ ነው።

566

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 11/2013 ዓ.ም (አብመድ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዲስ መልክ ሊደራጅ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲ አማካሪ
ማሞ ምህረቱ ገለጹ። አቶ ማሞ ለኢዜአ እንዳሉት በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪው ለኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ነው።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 60 በመቶ ተቀማጭ በመሰብሰብ በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ከፍተኛ ድርሻ ይይዛልም ነው ያሉት። የባንኩን አሰራር የበለጠ ለማሻሻልና የኢኮኖሚውን ዕድገት ለማሳለጥ አደረጃጀቱ ጥናት ተደርጎበት ሊቀየር መሆኑን ገልጸዋል።

እንደ አቶ ማሞ ገለጻ በ2012 ዓ.ም አብዛኞቹ ባንኮች የጥሬ ብር እጥረት አጋጥሟቸዋል። የገንዘብ ኖቶች ቅያሬውን ተከትሎ በርካታ ገንዘብ ወደ ባንክ መሰብሰብ በመቻሉ ለኢኮኖሚው የሚሰጠው ብድር ከፍ ማለቱንም አንስተዋል።

በተያዘው ዓመት የባንኮችን ተቀማጭ ገንዘብ በ24 በመቶ ለማሳደግ መታቀዱንና ለኢኮኖሚው 25 በመቶ ያደገ ብድር ለማሰራጨት መታሰቡን ጠቅሰው፣ ይህን ለማድረግ አስቻይ ሁኔታዎች መኖራቸውን ተናግረዋል።

ባለፈው ዓመት ባንኮች ለኢኮኖሚው ካሰራጩት 271 ቢሊዮን ብር 70 በመቶው ለግል ዘርፍ የተሰጠ ነው።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየፌዴሬሽን ምክር ቤት 15ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን አከባበር ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየመከረ ነው፡፡
Next articleበኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር 2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሀብቶች የሆቴል ኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጠ፡፡