በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ለመታደግ የደረሱ ሰብሎችን በመተጋገዝ መሰብሰብ ተጀምሯል።

255

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 11/2013 (አብመድ) በአስተዳደሩ ትናንት 9:00 ጀምሮ በጻግብጂ 02፣07፣08 እና 09 ቀበሌዎች፣ በሰቆጣ ወረዳ 07 እና 015 ቀበሌዎች የአንበጣ መንጋ ተከስቷል።

የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል በዘመናዊና ባህላዊ መንገድ ከሌሊቱ 6:00 ጀምሮ ርብርብ እየተደረገ ነው።

በሌላ መልኩ የአንበጣ መንጋው በተከሰተባቸው ቀበሌዎችና ሌሎች ሁሉም የአስተዳደሩ አካባቢዎች የደረሱ ሰብሎችን በርብርብ የመሰብሰብ ሥራ እየተሠራ መሆኑን የአስተዳደሩ ግብርና መምሪያ የሰብል ልማት ቡድን አስተባባሪ በዛብህ ጌታሁን ተናግረዋል።

በሰቆጣ ከተማም የአቅመ ደካሞች፣ የቤተ እምነት ተቋማት ሰብሎችን የክልሉ ልዮ ኃይል አባላትና ከኅብረተሰቡ የተወጣጡ ሰዎች እየሰበሰቡ ነው።

አቶ በዛብህ ጌታሁን የተከሰተውን አንበጣ ለመከላከል ከሚደረገው ርብርብ ጎንለጎን የደረሱ ሰብሎችን በጋራ የመሰብሰብ ዘመቻ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በዘንድሮው የመኸር ወቅት ከ120 ሺህ 600 ሄክታር በላይ ማሳ በሰብል ተሸፍኖ ነበር። ከተሸፈነው ውስጥ እስከ ዛሬ ድረስ ከ39 ሺህ 500 ሄክታር በላይ ሰብል መሰብሰቡንም አቶ በዛብህ ተናግረዋል።

ብሔረሰብ አስተዳደሩ ከአንበጣ ስጋቱ ውጭ ከዘንድሮ የሰብል ምርት 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት ማቀዱ ይታወሳል።

ዘጋቢ ፦ ግርማ ተጫነ

ፎቶ፦ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር
ኮሙዩኒኬሽን

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየጆርጂያዋ አትላንታ እና የሰሜን ወሎዋ ወልድያ፡ የሁለት ከተሞች የትብብር ወግ!
Next articleጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ (ዶክተር) የማክሮ-ኢኮኖሚ ኮሚቴ ጋር ተወያዩ።